Post Jobs

40/60 20/80 Real Estate Project Winers

40/60 20/80 Real Estate Project Winers

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር 51229 የ20/80ና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላለፈ
************************************************
በአዲስ አበባ የ13ኛ ዙር የ20/80 እና የ2ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በስነስርዓቱም ላይ የመዲናው ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት መስዋዕትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡

በዚህም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ሲባል ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ያለእጣ ቤት እንዲሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር አቶ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው በሀገሪቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የፍላጎቱና አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ባይሆንም የዘርፉ ልማት ስኬታማ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ልማት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ውጤታማ እንደሆነች እንደማሳያ ጠቁመዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ለዜጎች የመጠለያ ቤት ከማቅረብ ባለፈ የስራ እድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደፈጠረ ተናግረዋል አቶ ዣንጥራር፡፡

በቀጣይ የዘርፉ ልማት በመንግስት ብቻ መስራት ውጤታማ ስለማያደርግ የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ ተገቢ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ሚንስትሩ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ፍትሃዊ እንዲሆንም ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን የማጣራት ስራ ተሰርቶ እንዲሻሻል መደረጉንም ገልጸዋል፡፡